ኤርምያስ 35:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ፣ በኢዮአቄም ዘመነ መንግሥት፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንዲህ የሚል ቃል ወደ ኤርምያስ መጣ፤

2. “ወደ ሬካባውያን ሄደህ ወደ እግዚአብሔር ቤት አምጣቸው፤ ወደ አንዱም ክፍል አስገብተህ የሚጠጡትን ወይን ጠጅ ስጣቸው።”

3. ስለዚህ የካባስን ልጅ የኤርምያስን ልጅ ያእዛንያን፣ ወንድሞቹንና ወንዶች ልጆቹን ሁሉ፣ የሬካባውያንን ወገን በአጠቃላይ ሄጄ ጠራኋቸው፤

ኤርምያስ 35