ኤርምያስ 31:19-22 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

19. ከአንተ ከራቅሁ በኋላ፣ተመልሼ ተጸጸትሁ፤ባስተዋልሁም ጊዜ፣ጭኔን መታሁ፣የወጣትነት ውርደቴን ተሸክሜአለሁና፣ዐፈርሁ፤ ቀለልሁም።’

20. ኤፍሬም የምወደው፣ደስም የምሰኝበት ልጄ አይደለምን?ብዙ ጊዜ ተቃውሜው ብናገርም፣መልሼ ስለ እርሱ አስባለሁ፤አንጀቴ ይላወሳል፤በታላቅ ርኅራኄም እራራለታለሁ፤”ይላል እግዚአብሔር።

21. “የጐዳና ምልክት አቁሚ፤መንገድ አመልካች ትከዪ፤የምትሄጂበትን መንገድ፣አውራ ጐዳናውን አስተውዪ፤ድንግሊቱ እስራኤል ሆይ፤ ተመለሺ፤ወደ ከተሞችሽም ግቢ።

22. አንቺ ከዳተኛ ልጅ ሆይ፤እስከ መቼ ትቅበዘበዣለሽ? እግዚአብሔር በምድር ላይ አዲስ ነገር ይፈጥራል፤ሴት በወንድ ላይ ከበባ ታደርጋለች።

ኤርምያስ 31