ኤርምያስ 30:22-24 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

22. “ ‘ስለዚህ እናንተ ሕዝብ ትሆኑኛላችሁ፤እኔም አምላክ እሆናችኋለሁ።’ ”

23. እነሆ፣ የእግዚአብሔር ማዕበል፣በቍጣ ይነሣል፤የሚገለባብጥም ዐውሎ ነፋስ፣በክፉዎች ዐናት ላይ ይወርዳል።

24. የልቡን ሐሳብ ሳይፈጽም፣ የእግዚአብሔር ቍጣ፣እንዲሁ አይመለስም፤በሚመጡትም ዘመናት፣ይህን ታስተውላላችሁ።

ኤርምያስ 30