ኤርምያስ 30:1-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው፤

2. “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘የነገርሁህን ቃል ሁሉ በመጽሐፍ ጻፈው።

3. እነሆ፣ ሕዝቤን እስራኤልንና ይሁዳን’ ይላል እግዚአብሔር፤ ‘ለአባቶቻቸው ወደ ሰጠኋት ምድር የምመልስበት ጊዜ ተቃርቦአል፤ እነርሱም ይወርሷታል’ ይላል እግዚአብሔር።”

4. እግዚአብሔር ስለ እስራኤልና ስለ ይሁዳ የተናገረው ቃል ይህ ነው፤

5. “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ ‘የፍርሀትና የሽብር ጩኸት ተሰምቶአል፤ሰላምም የለም።

6. እስቲ ጠይቁ፤ ተመልከቱም፤ወንድ መውለድ ይችላል?ታዲያ ወንድ ሁሉ ምጥ እንደ ያዛት ሴት፣እጁን በሆዱ ላይ አድርጎ፣የሰውስ ሁሉ ፊት ጠቍሮ የማየው ለምንድን ነው?

7. ያ ቀን ምንኛ አስጨናቂ ይሆናል!እንደዚያም ያለ አይኖርም፤ለያዕቆብ የመከራ ጊዜ ነው፤ነገር ግን ይተርፋል።

8. “ ‘በዚያን ቀን’ ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤‘በጫንቃቸው ላይ ያለውን ቀንበር እሰብራለሁ፤እስራታቸውንም እበጥሳለሁ፤ከእንግዲህ ባዕዳን አይገዙአቸውም።

9. ነገር ግን ለአምላካቸው ለእግዚአብሔር፣ለማስነሣላቸውም ለንጉሣቸው፣ለዳዊት ይገዛሉ።

ኤርምያስ 30