ኤርምያስ 30:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው፤

2. “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘የነገርሁህን ቃል ሁሉ በመጽሐፍ ጻፈው።

3. እነሆ፣ ሕዝቤን እስራኤልንና ይሁዳን’ ይላል እግዚአብሔር፤ ‘ለአባቶቻቸው ወደ ሰጠኋት ምድር የምመልስበት ጊዜ ተቃርቦአል፤ እነርሱም ይወርሷታል’ ይላል እግዚአብሔር።”

4. እግዚአብሔር ስለ እስራኤልና ስለ ይሁዳ የተናገረው ቃል ይህ ነው፤

5. “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ ‘የፍርሀትና የሽብር ጩኸት ተሰምቶአል፤ሰላምም የለም።

ኤርምያስ 30