ኤርምያስ 29:28-32 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

28. ይህ ሰው፣ ‘የምርኮው ጊዜ ረዥም ስለ ሆነ፣ ቤት ሠርታችሁ ተቀመጡ፤ አትክልትም ተክላችሁ ፍሬውን ብሉ’ በማለት ወደ ባቢሎን መልእክት ልኮብናል።” ’ ”

29. ካህኑ ሶፎንያስም ደብዳቤውን ለነቢዩ ኤርምያስ አነበበለት።

30. የእግዚአብሔርም ቃል ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፤

31. “ይህን መልእክት በምርኮ ላሉት ሁሉ እንዲህ ብለህ ላክ፤ ‘ስለ ኔሔላማዊው ስለ ሸማያ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እኔ ሳልልከው ሸማያ ትንቢት ተናግሮላችሁ፣ በሐሰት እንድትታመኑ አድርጐአችኋልና፣

32. እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፤ ኔሔላማዊውን ሸማያንና ዘሩን እቀጣለሁ፤ በእኔ ላይ ዐመፅን ተናግሮአልና፣ በዚህ ሕዝብ መካከል የሚተርፍ ዘር አይኖረውም” ’ ይላል እግዚአብሔር፤ ‘ለሕዝቤ የማደርገውንም መልካም ነገር አያይም።’ ”

ኤርምያስ 29