ኤርምያስ 25:35-38 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

35. እረኞች የሚሸሹበት፣የመንጋ ጠባቂዎችም የሚያመልጡበት የለም።

36. እግዚአብሔር ማሰማሪያቸውን አጥፍቶአልና፣የእረኞችን ጩኸት፣የመንጋ ጠባቂዎችን ዋይታ ስሙ።

37. ከእግዚአብሔር ጽኑ ቍጣ የተነሣ፣ሰላማዊው ምድር ባድማ ይሆናል።

38. እንደ አንበሳ ከጐሬው ይወጣል፤ከአስጨናቂው ሰይፍ፣ከቍጣውም የተነሣ፣ምድራቸው ባድማ ትሆናለች።

ኤርምያስ 25