ኤርምያስ 25:14-17 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

14. ሕዝቧም ለብዙ ሕዝቦችና ለታላላቅ ነገሥታት ባሮች ይሆናሉ፤ እንደ አድራጎታቸውና እንደ እጃቸውም ሥራ እከፍላቸዋለሁ።”

15. የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፤ “በቍጣዬ የወይን ጠጅ የተሞላውን ይህን ጽዋ ከእጄ ውሰድ፤ እኔ ወደ ምልክህም ሕዝቦች ሁሉ ሄደህ አጠጣቸው።

16. በጠጡም ጊዜ ይንገዳገዳሉ፤ በመካከላቸው ከምሰደው ሰይፍ የተነሣ ያብዳሉ።”

17. ስለዚህ ጽዋውን ከእግዚአብሔር እጅ ተቀብዬ እርሱ ወደ ላከኝ ሕዝቦች ሁሉ ሄድሁ፤ እንዲጠጡትም አደረግሁ፤

ኤርምያስ 25