ኤርምያስ 18:14-16 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

14. የሊባኖስ ተራራ ድንጋያማ ተረተር፣በረዶ ተለይቶት ያውቃልን?ከጋራው የሚወርደውስ ቀዝቃዛ ውሃ፤መፍሰሱን ያቋርጣልን?

15. ሕዝቤ ግን ረስቶኛል፤ለማይረቡ ነገሮች ዐጥኖአል፣በራሱ መንገድ፣በቀደሞው ጐዳና ተሰናክሎአል፤በሻካራው መሄጃ፣ባልቀናውም ጥርጊያ መንገድ ሄዶአል።

16. ምድራቸው ባድማ፣ለዘላለም መሣለቂያ ይሆናል፤በዚያ የሚያልፍ ሁሉ ይደነቃል፤በመገረምም ራሱን ይነቀንቃል።

ኤርምያስ 18