15. እነርሱ ደጋግመው፣“የእግዚአብሔር ቃል የት አለ?እስቲ አሁን ይፈጸም!” ይሉኛል።
16. እረኛ ሆኜ አንተን ከማገልገል ወደ ኋላ አላልሁም፤ክፉ ቀን እንዳልተመኘሁ ታውቃለህ፤ከአንደበቴ የሚወጣውም በፊትህ ግልጽ ነው።
17. አስደንጋጭ አትሁንብኝ፤በመከራ ቀን መሸሸጊያዬ አንተ ነህ።
18. አሳዳጆቼ ይፈሩ፤እኔን ግን ከዕፍረት ጠብቀኝ፤እነርሱ ይደንግጡ፤እኔን ግን ከድንጋጤ ሰውረኝ፤ክፉ ቀን አምጣባቸው፤በዕጥፍ ድርብ ጥፋት አጥፋቸው።
19. እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፤ “ሄደህ የይሁዳ ነገሥታት በሚገቡበትና በሚወጡበት በሕዝቡ በር በሌሎቹም የኢየሩሳሌም በሮች ሁሉ ቁም፤
20. እንዲህም በላቸው፤ ‘በእነዚህ በሮች የምትገቡ የይሁዳ ነገሥታት ሆይ፤ የይሁዳ ሕዝብና በኢየሩሳሌም የምትኖሩ ሁሉ፤ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።
21. እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “በሰንበት ቀን ሸክም ተሸክማችሁ በኢየሩሳሌም በሮች እንዳታስገቡ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።
22. አባቶቻችሁን እንዳዘዝኋቸው ሰንበትን አክብሩ እንጂ በሰንበት ቀን ከየቤታችሁ ሸክም ይዛችሁ አትውጡ፤ ምንም ሥራ አትሥሩ።”
23. እነርሱ ግን አልሰሙም፤ ልብም አላሉም፤ እንዳይሰሙና እንዳይገሠጹም ዐንገታቸውን አደነደኑ።