14. እግዚአብሔር ሆይ፤ ፈውሰኝ፤ እፈወሳለሁ፤አድነኝ እኔም እድናለሁ፤አንተ ምስጋናዬ ነህና።
15. እነርሱ ደጋግመው፣“የእግዚአብሔር ቃል የት አለ?እስቲ አሁን ይፈጸም!” ይሉኛል።
16. እረኛ ሆኜ አንተን ከማገልገል ወደ ኋላ አላልሁም፤ክፉ ቀን እንዳልተመኘሁ ታውቃለህ፤ከአንደበቴ የሚወጣውም በፊትህ ግልጽ ነው።
17. አስደንጋጭ አትሁንብኝ፤በመከራ ቀን መሸሸጊያዬ አንተ ነህ።
18. አሳዳጆቼ ይፈሩ፤እኔን ግን ከዕፍረት ጠብቀኝ፤እነርሱ ይደንግጡ፤እኔን ግን ከድንጋጤ ሰውረኝ፤ክፉ ቀን አምጣባቸው፤በዕጥፍ ድርብ ጥፋት አጥፋቸው።
19. እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፤ “ሄደህ የይሁዳ ነገሥታት በሚገቡበትና በሚወጡበት በሕዝቡ በር በሌሎቹም የኢየሩሳሌም በሮች ሁሉ ቁም፤
20. እንዲህም በላቸው፤ ‘በእነዚህ በሮች የምትገቡ የይሁዳ ነገሥታት ሆይ፤ የይሁዳ ሕዝብና በኢየሩሳሌም የምትኖሩ ሁሉ፤ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።