ኤርምያስ 14:5-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. አንዳች ሣር ባለመኖሩ፣የሜዳ አጋዘን እንኳ፣እንደ ወለደች ግልገሏን ጥላ ትሄዳለች።

6. የሜዳ አህዮች ባድማ ኰረብቶች ላይ ቆሙ፤እንደ ቀበሮም አየር ፍለጋ አለከለኩ፤ግጦሽ ባለመገኘቱ፣ዐይኖቻቸው ፈዘዙ።”

7. እግዚአብሔር ሆይ፤ ከአንተ መኰብለል አብዝተናል፤በአንተም ላይ ዐምፀናል፤ኀጢአታችን ቢመሰክርብንም እንኳ፣ስለ ስምህ ብለህ አንድ ነገር አድርግልን።

8. አንተ የእስራኤል ተስፋ፤በጭንቀት ጊዜ አዳኙ፣ለምን በምድሪቱ እንደ ባዕድ፣እንደ ሌት አዳሪ መንገደኛ ትሆናለህ?

ኤርምያስ 14