ኤርምያስ 14:16-18 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

16. ትንቢቱ የተነገረለትም ሕዝብ ከሰይፍና ከራብ የተነሣ በኢየሩሳሌም አደባባዮች ይወድቃል፤ እነርሱንም ሆነ ሚስቶቻቸውን ወይም ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን የሚቀብራቸው አይገኝም። ለበደላቸው የሚገባውንም ቅጣት በላያቸው አወርዳለሁ።

17. “ይህን ቃል እንዲህ ብለህ ንገራቸው፤“ ‘ድንግሊቱ ልጄ፣ ሕዝቤ፣በታላቅ ስብራት፣በብርቱ ቍስል ተመትታለችናዐይኖቼ ቀንና ሌሊት፣ ሳያቋርጡእንባ ያፈስሳሉ

18. ወደ ገጠር ብወጣ፣በሰይፍ የተገደሉትን አያለሁ፤ወደ ከተማ ብገባ፣ በራብ የወደቁትን አያለሁነቢዩም ካህኑም፣ወደማያውቁት አገር ሸሽተዋል።’ ”

ኤርምያስ 14