ኤርምያስ 13:4-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. “ገዝተህ የታጠቅህበትን መቀነት ይዘህ፣ ወደ ኤፍራጥስ ሂድ፤ በዚያም በዐለት ንቃቃት ውስጥ ሸሽገው።”

5. ስለዚህ እግዚአብሔር በነገረኝ መሠረት ወደ ኤፍራጥስዠ ሄጄ ሸሸግሁት።

6. ከብዙ ቀን በኋላም እግዚአብሔር፣ “ተነሥተህ ወደ ኤፍራጥስ ሂድ፤ በዚያ እንድት ሸሽገው የነገርሁህን መቀነት አምጣ” አለኝ።

7. እኔም ወደ ኤፍራጥስ ሄጄ፤ መታጠቂያውን ከሸሸግሁበት ቦታ ቈፍሬ አወጣሁ፤ መታጠቂያውም ተበላሽቶ፣ ከጥቅም ውጭም ሆኖ ነበር።

8. የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፤

9. “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘የይሁዳን ትዕቢትና የኢየሩሳሌምን እብሪት እንደዚሁ አጠፋለሁ።

ኤርምያስ 13