ኤርምያስ 13:19-23 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

19. በኔጌቭ ያሉ ከተሞች ይዘጋሉ፤የሚከፍታቸውም አይኖርም፤ይሁዳ ሁሉ ተማርኮ ይሄዳል፤ሙሉ በሙሉም ይዘጋል።

20. ዐይኖቻችሁን ከፍታችሁ፣ከሰሜን የሚመጡትን እዩ።ለአንቺ የተሰጠው መንጋ፣የተመካሽባቸው በጎች የት አሉ?

21. ልዩ ወዳጆች እንዲሆኑሽያስተማርሻቸው፣ባለ ሥልጣን ሲሆኑብሽ ምን ትያለሽ?እንደምትወልድ ሴት፣ምጥ አይዝሽምን?

22. “ይህ ለምን ደረሰብኝ?” ብለሽራስሽን ብትጠይቂ፣ልብስሽን ተገልበሽ የተገፈተርሽው፣በሰውም እጅ የተንገላታሽው፣ከኀጢአትሽ ብዛት የተነሣ ነው።

23. ኢትዮጵያዊ መልኩን፣ነብርስ ዝንጒርጒርነቱን መለወጥ ይችላልን?እናንት ክፉ ማድረግ የለመዳችሁትም፣መልካም ማድረግ አትችሉም።

ኤርምያስ 13