ኤርምያስ 10:7-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. የሕዝቦች ሁሉ ንጉሥ ሆይ፤አንተን የማይፈራ ማነው?ክብር ይገባሃልና።ከምድር ጠቢባን ሁሉ፣ከመንግሥቶቻቸውም ሁሉ መካከል፣እንዳንተ ያለ የለም።

8. ከከንቱ የዕንጨት ጣዖት ትምህርት የሚቀስሙ ሁሉ፣ጅሎችና ሞኞች ናቸው።

9. የተጠፈጠፈ ብር ከተርሴስ፣ወርቅም ከአፌዝ ይመጣል።ባለሙያውና አንጥረኛው የሠሯቸው፣ብልኀተኞችም ያበጇቸው ሁሉ፣ሰማያዊና ሐምራዊ ልብስ ተጐናጽፈዋል።

10. እግዚአብሔር ግን እውነተኛ አምላክ ነው፤እርሱ ሕያው አምላክ፣ ዘላለማዊም ንጉሥ ነው፤በሚቈጣበት ጊዜ ምድር ትንቀጠቀጣለች፤መንግሥታትም ቍጣውን ሊቋቋሙ አይችሉም።

ኤርምያስ 10