4. ልጆችህ በእርሱ ላይ ኀጢአት ሠርተው ከሆነ፣ለኀጢአታቸው ቅጣት አሳልፎ ሰጥቶአቸዋል።
5. ነገር ግን አንተ ወደ እግዚአብሔር ብትመለከት፣ሁሉን ቻይ አምላክን ብትማፀን፣
6. ንጹሕና ቅን ብትሆን፣ እርሱ ስለ አንተ አሁኑኑ ይነሣል፤ወደ ተገቢውም ስፍራህ ይመልስሃል።
7. ጅማሬህ አነስተኛ ቢመስልም፣ፍጻሜህ እጅግ ታላቅ ይሆናል።
8. “የቀደመውን ትውልድ ጠይቅ፤አባቶቻቸውም የደረሱበትን መርምረህ አግኝ፤
9. እኛ ትናንት ስለ ተወለድን አንዳች አናውቅምና፤ዘመናችንም በምድር ላይ እንደ ጥላ ነው።
10. እነርሱ የሚያስተምሩህና የሚነግሩህ፣ከልቦናቸውም ቃልን የሚያወጡ አይደሉምን?