13. አልጋዬ ያጽናናኛል፣መኝታዬም ማጒረምረሜን ይቀንስልኛል ባልሁ ጊዜ፣
14. አንተ በሕልም ታስፈራራኛለህ፤በራእይም ታስደነግጠኛለህ፤
15. ስለዚህ እንዲህ ሆኖ ከመኖር፣መታነቅና መሞትን እመርጣለሁ።
16. ሕይወቴን እጸየፋለሁ፤ ዘላለም መኖር አልፈልግም፣ዘመኔ እንደ እስትንፋስ ነውና ተወኝ።
17. “ከፍ ከፍ ታደርገው ዘንድ፣ልብህንም ትጥልበት ዘንድ ሰው ምንድን ነው?
18. በየማለዳው ትመረምረዋለህ፤በየጊዜውም ትፈትነዋለህ።
19. ዐይንህን ከእኔ ላይ አታነሣምን?ምራቄን እንኳ እስክውጥ ፋታ አትሰጠኝምን?
20. ሰውን የምትከታተል ሆይ፤ኀጢአት ብሠራ፣ አንተን ምን አደርግሃለሁ?ለምን ዒላማህ አደረግኸኝ?ለምንስ ሸክም ሆንሁብህ?
21. መተላለፌን ለምን ይቅር አትልም?ኀጢአቴንስ ለምን አታስወግድልኝም?ትቢያ ውስጥ የምጋደምበት ጊዜ ደርሶአል፤ትፈልገኛለህ፤ እኔ ግን የለሁም።”