ኢዮብ 6:4-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. ሁሉን የሚችል አምላክ ፍላጻ በውስጤ ነው፤መንፈሴም መርዙን ትጠጣለች፤የእግዚአብሔር ማስደንገጥ ተሰልፎብኛል።

5. የሜዳ አህያ ሣር እያለው፣በሬስ ድርቆሽ እያለው፣ ይጮኻልን?

6. የማይጣፍጥ ምግብ ያለ ጨው ይበላልን?ወይስ የዕንቍላል ውሃ ጣዕም አለውን?

ኢዮብ 6