ኢዮብ 6:17-25 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

17. በበጋ ወራት ግን ይጠፋል፤በሙቀትም ጊዜ መፋሰሻው ላይ አይገኝም።

18. ሲራራ ነጋዴዎች ውሃ አጥተው መንገዳቸውን ይቀይራሉ፤ወደ በረሓም ገብተው ይጠፋሉ።

19. የቴማን ነጋዴዎች ውሃ ይፈልጋሉየሳባ መንገደኞችም ተስፋ ያደርጋሉ፤

20. እርግጠኞች ሆነው ስለ ነበር ተሰቀቁ፤እዚያ ደረሱ፣ ግን ዐፈሩ።

21. አሁንም እናንተ እንደዚያ ሆናችሁብኝ፣መከራዬን አይታችሁ ፈራችሁ።

22. ለመሆኑ፣ ‘ስለ እኔ ሆናችሁ አንድ ነገር ስጡልኝ፣በዕዳ የተያዘብኝንም በሀብታችሁ አስለቅቁልኝ!’ ብያለሁን?

23. ወይስ፤ ‘ከጠላት አስጥሉኝ፤ከጨካኝም እጅ ተቤዡኝ’ አልኋችሁን?

24. “አስተምሩኝ፤ እኔም ዝም እላለሁ፤ምኑ ላይ እንደ ተሳሳትሁ ጠቍሙኝ።

25. የቅንነት ቃል ምንኛ ኀያል ነው!የእናንተ ክርክር ግን ምን ፋይዳ አለው?

ኢዮብ 6