ኢዮብ 5:10-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

10. ምድሪቱን በዝናብ ያረሰርሳል፤ሜዳውንም ውሃ ያጠጣል።

11. የተዋረዱትን በከፍታ ቦታ ያስቀምጣል፤ያዘኑትንም ወደ አስተማማኝ ስፍራ ያወጣቸዋል።

12. እጃቸው ያሰቡትን እንዳይፈጽም፣የተንኰለኞችን ዕቅድ ያከሽፋል።

13. ጠቢባንን በጥበባቸው ይይዛል፤የተንኰለኞችንም ሤራ ያጠፋል።

14. ቀኑ ጨለማ ይሆንባቸዋል፤በቀትርም ጊዜ በሌሊት እንዳለ ሰው በዳበሳ ይሄዳሉ።

ኢዮብ 5