1. ኢዮብም እንዲህ ሲል ለእግዚአብሔር መለሰ፤
2. “አንተ ሁሉን ማድረግ እንደምትችል፣ዕቅድህም ከቶ እንደማይሰናከል ዐወቅሁ።
3. አንተ፣ ‘ያለ ዕውቀት ዕቅዴን የሚያደበዝዝ ይህ ማን ነው’ አልኸኝ፤በእርግጥ ያልገባኝን ነገር፣የማላውቀውንና ላስተውለው የማልችለውን ጒዳይ ተናገርሁ።
4. “ ‘ስማኝ፣ ልናገር እኔ እጠይቃለሁ፤አንተ ትመልስልኛለህ’ አልኸኝ።
5. ጆሮዬ ስለ አንተ ሰምታ ነበር፤አሁን ግን ዐይኔ አየችህ።
6. ስለዚህ ራሴን እንቃለሁ፤በትቢያና በዐመድ ላይ ተቀምጬ ንስሓ እገባለሁ።”