ኢዮብ 41:31-34 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

31. እንደሚፈላ ምንቸት ጥልቁን ያናውጠዋል፤ባሕሩንም እንደ ሽቶ ብልቃጥ ያደርገዋል።

32. ያለፈበትን መንገድ ብሩህ ያደርጋል፤ቀላዩንም ሽበት ያወጣ ያስመስለዋል።

33. ያለ ፍርሀት የተፈጠረ፣እንደ እርሱ ያለ በምድር ላይ የለም።

34. ከፍ ያሉትን ሁሉ በንቀት ይመለከታል፤በትዕቢተኞችም ሁሉ ላይ ንጉሥ ነው።”

ኢዮብ 41