ኢዮብ 41:13-22 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

13. የደረበውን ልብስ ማን ሊያወልቅ ይችላል?ማንስ ሊለጒመው ወደ መንጋጋው ይቀርባል?

14. አስፈሪ ጥርሶቹ የተገጠገጡበትን፣የአፉን ደጅ ማን ደፍሮ ይከፍታል?

15. ጀርባው፣ አንድ ላይ የተጣበቁ፣የጋሻ ረድፎች አሉት፤

16. እጅግ የተቀራረቡ ስለሆኑ፣ነፋስ በመካከላቸው አያልፍም፤

17. እርስ በርስ የተገጣጠሙ ናቸው፤አንዱ ከአንዱ ጋር ተጣብቆአልና ማንም ሊለያያቸው አይችልም።

18. እንጥሽታው የብርሃን ብልጭታ ያወጣል፤ዐይኖቹም እንደ ማለዳ ጮራ ናቸው።

19. ከአፉ ፍም ይወጣል፤የእሳት ትንታግ ይረጫል።

20. በሸምበቆ ማገዶ ላይ ከተጣደ ድስት እንደሚወጣ እንፋሎት፣ከአፍንጫው ጢስ ይትጐለጐላል።

21. እስትንፋሱ ከሰል ያቀጣጥላል፤የእሳትም ነበልባል ከአፉ ይወጣል።

22. ብርታት በዐንገቱ ውስጥ አለ፤አሸባሪነትም በፊቱ እመር እመር ይላል።

ኢዮብ 41