ኢዮብ 40:5-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. አንድ ጊዜ ተናገርሁ፤ የምመልሰው የለኝም፤ሁለተኛም ተናገርሁ፤ ከእንግዲህ አንዳች አልጨምርም።”

6. እግዚአብሔርም በዐውሎ ነፋስ ውስጥ ሆኖ፣ ለኢዮብ እንዲህ ሲል ተናገረ፤

7. “እንግዲህ እንደ ወንድ ወገብህን ታጠቅ፤እኔ እጠይቅሃለሁ፤አንተም መልስልኝ።

8. “ፍርዴን ታቃልላለህን?ወይስ አንተ ጻድቅ ለመሆን እኔን ትኰንናለህ?

9. እንደ እግዚአብሔር ክንድ ያለ ክንድ አለህን?ድምፅህስ እንደ እርሱ ድምፅ ሊያንጐደጒድ ይችላልን?

10. እንግዲያስ ክብርንና ልዕልናን ተጐናጸፍ፤ግርማ ሞገስንም ተላበስ፤

ኢዮብ 40