ኢዮብ 40:4-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. “እኔ ከንቱ ሰው፣ ምን እመልስልሃለሁ?እጄን በአፌ ላይ እጭናለሁ።

5. አንድ ጊዜ ተናገርሁ፤ የምመልሰው የለኝም፤ሁለተኛም ተናገርሁ፤ ከእንግዲህ አንዳች አልጨምርም።”

6. እግዚአብሔርም በዐውሎ ነፋስ ውስጥ ሆኖ፣ ለኢዮብ እንዲህ ሲል ተናገረ፤

7. “እንግዲህ እንደ ወንድ ወገብህን ታጠቅ፤እኔ እጠይቅሃለሁ፤አንተም መልስልኝ።

8. “ፍርዴን ታቃልላለህን?ወይስ አንተ ጻድቅ ለመሆን እኔን ትኰንናለህ?

ኢዮብ 40