ኢዮብ 40:11-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. ቍጣህን አፍስስ፤ትዕቢተኛውን ሁሉ ተመልክተህ አዋርደው፤

12. ትዕቢተኛውን ሰው ሁሉ ተመልክተህ ዝቅ አድርገው፤ክፉዎችንም በቆሙበት ስፍራ አድቅቃቸው።

13. ሁሉንም በአንድ ላይ ከዐፈር ደባልቃቸው፤ፊታቸውንም በመቃብር ውስጥ ሸፍን።

14. እኔም ቀኝ እጅህ እንደምታድንህ፣በዚያን ጊዜ አረጋግጬ እቀበላለሁ።

ኢዮብ 40