ኢዮብ 4:4-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. ቃልህ የተሰናከሉትን ያነሣ ነበር፤የሚብረከረከውንም ጒልበት ታጸና ነበር።

5. አሁን ግን መከራ አገኘህ፣ አንተም ተስፋ ቈረጥህ፤ሸነቈጠህ፤ ደነገጥህም።

6. እግዚአብሔርን መፍራት መታመኛህ፣ቀና አካሄድህም ተስፋህ አይደለምን?

7. “አሁንም አስተውል፤ ንጹሕ ሆኖ የጠፋ፣ ማን ነው?ቅኖችስ መች ተደምስሰው ያውቃሉ?

ኢዮብ 4