ኢዮብ 39:11-15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. ጒልበቱ ብርቱ ስለ ሆነ ትተማመንበታለህ?ከባዱን ሥራህንስ ለእርሱ ትተዋለህ?

12. እህልህን እንዲሰበስብልህ፣በዐውድማህም ላይ እንዲያከማችልህ ታምነዋለህን?

13. “ሰጎን ክንፎቿን በደስታ ታራግባለች፤ነገር ግን እንደ ሽመላ ላባዎች ሊሆኑ አይችሉም።

14. ዕንቍላሏን መሬት ላይ ትጥላለች፤እንዲሞቅም በአሸዋ ውስጥ ትተወዋለች።

15. እግር እንደሚሰብረው፤የዱር አውሬም እንደሚረግጠው አታስብም።

ኢዮብ 39