ኢዮብ 38:4-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. “ምድርን በመሠረትሁ ጊዜ አንተ የት ነበርህ?በእርግጥ የምታስተውል ከሆንህ፣ ንገረኝ።

5. ካወቅህ፣ መጠኗን ለይቶ ማን ወሰነ?በላይዋስ መለኪያ ገመድ የዘረጋ ማን ነው?

6. መሠረቶቿ ምን ላይ ተተከሉ?የማእዘን ድንጋይዋንስ ማን አቆመ?

7. ይህም የሆነው የንጋት ከዋክብት በዘመሩበት ጊዜ፣መላእክትም እልል ባሉበት ጊዜ ነበር።

8. “ባሕር ከማሕፀን በወጣ ጊዜ፣በር የዘጋበት ማን ነው?

ኢዮብ 38