ኢዮብ 38:3-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. እስቲ እንደ ወንድ ወገብህን ታጠቅ፤እኔ ልጠይቅህ፣አንተም መልስልኝ።

4. “ምድርን በመሠረትሁ ጊዜ አንተ የት ነበርህ?በእርግጥ የምታስተውል ከሆንህ፣ ንገረኝ።

5. ካወቅህ፣ መጠኗን ለይቶ ማን ወሰነ?በላይዋስ መለኪያ ገመድ የዘረጋ ማን ነው?

6. መሠረቶቿ ምን ላይ ተተከሉ?የማእዘን ድንጋይዋንስ ማን አቆመ?

ኢዮብ 38