ኢዮብ 37:4-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. ከዚያም በኋላ የድምፁ ጩኸት ይመጣል፤በድምፁም ግርማ ያንጐደጒዳል፤ድምጹ በተሰማ ጊዜ፣መብረቁን የሚከለክል የለም።

5. የእግዚአብሔር ድምፅ በሚያስደንቅ ሁኔታ ያንጐደጒዳል፤እኛ የማናስተውለውንም ታላቅ ነገር ያደርጋል።

6. በረዶውን፣ ‘በምድር ላይ ውደቅ’ውሽንፍሩንም ‘ዶፍህን አውርደው’ ይላል።

7. እርሱ የፈጠራቸው ሰዎች ሁሉ ሥራውን ያውቁ ዘንድ፣እያንዳንዱ ሰው እንዳይሠራ ይገታዋል።

8. እንስሳት ይጠለላሉ፤በየዋሻቸውም ይቈያሉ።

9. ዐውሎ ነፋስ ከማደሪያው፣ብርድም ከብርቱ ነፋስ ይወጣል።

10. የእግዚአብሔር እስትንፋስ በረዶ ያስገኛል፤ሰፋፊ ውሆች ግግር በረዶ ይሆናሉ።

ኢዮብ 37