ኢዮብ 37:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ልቤ በዚህ በኀይል ይመታል፤ከስፍራውም ዘለል ዘለል ይላል።

2. ስሙ! የድምፁን ጩኸት ስሙ፤ከአፉ የሚወጣውን ጒርምርምታ አድምጡ።

3. መብረቁን ከሰማይ ሁሉ በታች ያባርቃል፤ወደ ምድርም ዳርቻ ይልካል።

4. ከዚያም በኋላ የድምፁ ጩኸት ይመጣል፤በድምፁም ግርማ ያንጐደጒዳል፤ድምጹ በተሰማ ጊዜ፣መብረቁን የሚከለክል የለም።

5. የእግዚአብሔር ድምፅ በሚያስደንቅ ሁኔታ ያንጐደጒዳል፤እኛ የማናስተውለውንም ታላቅ ነገር ያደርጋል።

6. በረዶውን፣ ‘በምድር ላይ ውደቅ’ውሽንፍሩንም ‘ዶፍህን አውርደው’ ይላል።

ኢዮብ 37