ኢዮብ 36:15-18 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

15. ነገር ግን የሚሠቃዩትን ከሥቃያቸው ያድናቸዋል፤በመከራቸውም ውስጥ ይናገራቸዋል።

16. “አንተንም ከመከራ መንጋጋ፣ጭንቀት ወደሌለበት ወደ ሰፊ ስፍራ፣ምርጥ ምግብ ወደ ሞላበት ማእድ ያወጣሃል።

17. አሁን ግን ለክፉዎች የሚገባው ፍርድ በላይህ ተጭኖአል፤ፍርድና ብይን ይዘውሃል።

18. ባለጠግነት እንዳያታልልህ፣የእጅ መንሻ ብዛትም እንዳያስትህ ተጠንቀቅ።

ኢዮብ 36