ኢዮብ 35:2-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

2. “ ‘በእግዚአብሔር ፊት ንጹሕ ነኝ’ ማለትህ፣ትክክል ይመስልሃልን?

3. ደግሞ ‘ያገኘሁት ጥቅም ምንድን ነው?ኀጢአት ባለ መሥራቴስ ምን አተረፍሁ?’ ብለህ ጠይቀኸዋል።

4. “ለአንተና አብረውህ ላሉት ባልንጀሮችህ፣መልስ መስጠት እፈልጋለሁ።

5. ቀና ብለህ ወደ ሰማይ እይ፤ከአንተ በላይ ከፍ ብለው ያሉትንም ደመናት ተመልከት።

6. ኀጢአትህስ ቢበዛ እርሱን ምን ትጐዳዋለህ?ኀጢአትህስ ቢበዛ ምን ያደርገዋል?

7. ጻድቅ ብትሆንም ለእርሱ ምን ትሰጠዋለህ?ከእጅህስ ምን ይቀበላል?

8. ክፋትህ የሚጐዳው እንዳንተ ያለውን ሰው ብቻ ነው፤ጽድቅህም የሚጠቅመው የሰውን ልጆች ብቻ ነው።

ኢዮብ 35