ኢዮብ 34:33-37 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

33. ታዲያ አንተ ለመናዘዝ ፈቃደኛ ሳትሆን፤እግዚአብሔር እንደ ወደድህ ይከፍልሃልን?መወሰን ያለብህ አንተ ነህ እንጂ፣ እኔ አይደለሁም፤እንግዲህ የምታውቀውን ንገረኝ።

34. “አስተዋዮች ይናገራሉ፤የሚሰሙኝም ጠቢባን እንዲህ ይሉኛል፤

35. ‘ኢዮብ ያለ ዕውቀት ይናገራል፤ቃሉም ማስተዋል ይጐድለዋል።’

36. ምነው ኢዮብ እስከ መጨረሻ በተፈተነ ኖሮ!እንደ ክፉ ሰው መልሶአልና፤

37. በኀጢአቱም ላይ ዐመፅን ጨምሮአል፤በመካከላችን ሆኖ በንቀት አጨብጭቦአል፤በእግዚአብሔርም ላይ ብዙ ተናግሮአል።”

ኢዮብ 34