ኢዮብ 34:16-19 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

16. “ማስተዋል ካለህ ይህን ስማ፤እኔ የምለውንም አድምጥ።

17. ፍትሕን የሚጠላ ሊያስተዳድር ይችላልን?አንተስ ጻድቁንና ኀያል የሆነውን ትኰንናለህ?

18. ነገሥታትን ‘የማትረቡ ናችሁ፣’መኳንንትንም፣ ‘ክፉዎች ናችሁ’የሚላቸው እርሱ አይደለምን?

19. ሁሉም የእጁ ሥራ ስለሆኑ፣እርሱ ለገዦች አያደላም፤ባለጠጋውንም ከድኻው አብልጦ አይመለከትም።

ኢዮብ 34