ኢዮብ 33:27-33 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

27. ከዚያም ወደ ሰዎች መጥቶ እንዲህ ይላል፤‘ኀጢአትን ሠርቻለሁ፤ ትክክል የሆነውን አጣምሜአለሁ፤ነገር ግን የእጄን አላገኘሁም።

28. ነፍሴ ወደ ጒድጓድ እንዳትወርድ፣ታድጎአታል፤ በሕይወትም ሆኜ ብርሃን አያለሁ።’

29. “እግዚአብሔር ይህን ሁሉ፣ሁለት ሦስት ጊዜ ለሰው ያደርጋል።

30. ይኸውም የሕይወት ብርሃን ይበራለት ዘንድ፣ነፍሱን ከጒድጓድ ለመመለስ ነው።

31. “ኢዮብ ሆይ፤ ልብ ብለህ ስማኝ፤እኔ ልናገር፤ አንተ ዝም በል።

32. የምትለው ካለህ፣ መልስ ስጠኝ፤ትክክለኛነትህንም ማወቅ እፈልጋለሁና ተናገር፤

33. አለበለዚያ፣ ዝም ብለህ ስማኝ፤እኔም ጥበብን አስተምርሃለሁ።”

ኢዮብ 33