ኢዮብ 33:13-17 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

13. የሰውን አቤቱታ እንደማይሰማ፣ለምን ታማርርበታለህ?

14. ሰው ባያስተውለውም፣እግዚአብሔር በተለያየ መንገድ ይናገራል፤

15. ሰዎች ዐልጋቸው ላይ ተኝተው ሳሉ፣ከባድ እንቅልፍ ሲወድቅባቸው፣በሕልም፣ በሌሊትም ራእይ፣ ይናገራል።

16. በጆሯቸው ይናገራል፤በማስጠንቀቂያም ያስደነግጣቸዋል፤

17. ሰውን ከክፉ ሥራው ይመልሳል፤ከትዕቢት ይጠብቃል፤

ኢዮብ 33