ኢዮብ 33:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. “አሁን ግን ኢዮብ ሆይ፣ ንግግሬን ስማ፤የምለውንም ሁሉ አድምጥ።

2. እንግዲህ አፌን እከፍታለሁ፤አንደበቴም ይናገራል።

3. ቃሌ ከቅን ልብ ይወጣል፤ከንፈሬም የማውቀውን በትክክል ይናገራል።

4. የእግዚአብሔር መንፈስ ፈጥሮኛል፤ሁሉን የሚችለውም አምላክ እስትንፋስ ሕይወት ሰጥቶኛል።

ኢዮብ 33