ኢዮብ 31:6-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. እግዚአብሔር በእውነተኛ ሚዛን ይመዝነኝ፤ነውር እንደሌለብኝም ይወቅ።

7. አረማመዴ ከመንገድ ወጣ ብሎ፣ልቤ ዐይኔን ተከትሎ፣ወይም እጄ ረክሶ ከሆነ፣

8. የዘራሁትን ሌላ ይብላው፤ሰብሌም ተነቅሎ ይጥፋ።

9. “ልቤ ሌላዋን ሴት ከጅሎ፣በባልንጀራዬ ደጅ አድብቼ ከሆነ፣

10. ሚስቴ የሌላ ሰው እህል ትፍጭ፤ሌሎች ሰዎችም ይተኟት፤

11. ይህ አሳፋሪ፣ፍርድም የሚገባው ኀጢአት ነውና።

ኢዮብ 31