ኢዮብ 31:34-39 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

34. ሕዝቡን በመፍራት፣የወገኖቼንም ንቀት በመሸሽ፣ወደ ደጅ ሳልወጣ፣ ዝም ብዬ ቤት ውስጥ አልተቀመጥሁም።

35. “ምነው የሚሰማኝ ባገኝ!የመከላከያ ፊርማዬ እነሆ፤ ሁሉን የሚችል አምላክ ይመልስልኝ፤ከሳሼም ክሱን በጽሑፍ ያቅርብ።

36. በእርግጥ ትከሻዬ ላይ በደረብሁት፣እንደ አክሊልም ራሴ ላይ በደፋሁት ነበር።

37. እያንዳንዱን ርምጃዬን በገለጽሁለት፣እንደ ልዑል እየተንጐራደድሁ በቀረብሁት ነበር።

38. “ዕርሻዬ በእኔ ላይ ጮኻ ከሆነ፣ትልሞቿ ሁሉ በእንባ ርሰው እንደሆነ፣

39. ፍሬዋን ያለ ዋጋ በልቼ፣የባለመሬቶቿን ነፍስ አሳዝኜ ከሆነ፣

ኢዮብ 31