3. ለኀጢአተኞች ጥፋት፣ክፉ ለሚያደርጉም መቅሠፍት አይደለምን?
4. እርሱ መንገዴን አያይምን?እርምጃዬንስ ሁሉ አይቈጥርምን?
5. “በሐሰት ሄጄ እንደሆነ፣እግሬም ወደ ሽንገላ ቸኵሎ ከሆነ፣
6. እግዚአብሔር በእውነተኛ ሚዛን ይመዝነኝ፤ነውር እንደሌለብኝም ይወቅ።
7. አረማመዴ ከመንገድ ወጣ ብሎ፣ልቤ ዐይኔን ተከትሎ፣ወይም እጄ ረክሶ ከሆነ፣
8. የዘራሁትን ሌላ ይብላው፤ሰብሌም ተነቅሎ ይጥፋ።
9. “ልቤ ሌላዋን ሴት ከጅሎ፣በባልንጀራዬ ደጅ አድብቼ ከሆነ፣
10. ሚስቴ የሌላ ሰው እህል ትፍጭ፤ሌሎች ሰዎችም ይተኟት፤
11. ይህ አሳፋሪ፣ፍርድም የሚገባው ኀጢአት ነውና።
12. ይህ የሚያቃጥልና የሚያጠፋ እሳት ነው፤ቡቃያዬንም ባወደመ ነበር።
13. “ወንዶችና ሴቶች አገልጋዮቼ አቤቱታ ባቀረቡ ጊዜ፣ፍርድ አዛብቼ ከሆነ፣
14. እግዚአብሔር ሲነሣ ምን አደርጋለሁ?ሲጠይቀኝስ ምን መልስ እሰጣለሁ?