ኢዮብ 31:15-23 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

15. እኔን በማሕፀን ውስጥ የፈጠረኝ እነርሱን የፈጠረ አይደለምን?በሆድ ውስጥ የሠራንስ እርሱ ራሱ አይደለምን?

16. “ለድኻ የሚያስፈልገውን ከልክዬ ከሆነ፣ወይም የመበለቲቱን ዐይን አፍዝዤ ከሆነ፣

17. እንጀራዬን ከድኻ አደጉ ጋር ሳልካፈል፣ለብቻዬ በልቼ ከሆነ፣

18. ይልቁን ድኻ አደጉን ከታናሽነቴ ጀምሮ እንደ አባት አሳደግሁት፤መበለቲቱንም ከተወለድሁ ጀምሮ መንገድ መራኋት፤

19. በልብስ ዕጦት ሰው ሲጠፋ፣ወይም ዕርቃኑን ያልሸፈነ ድኻ አይቼ፣

20. በበጎቼ ጠጒር ስላሞቅሁት፣ልቡ ባርኮኝ ካልሆነ፣

21. በአደባባይ ተሰሚነት አለኝ ብዬ፣በድኻ አደጉ ላይ እጄን አንሥቼ ከሆነ፣

22. ትከሻዬ ከመጋጠሚያው ይነቀል፤ክንዴም ከመታጠፊያው ይሰበር፤

23. የእግዚአብሔርን ቍጣ በመፍራቴ፣እንዲህ ያሉ ነገሮች መፈጸም አልቻልሁም።

ኢዮብ 31