ኢዮብ 30:26-30 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

26. ነገር ግን መልካም ስጠብቅ፣ ክፉ ነገር ደረሰብኝ፤ብርሃንንም ስጠባበቅ፣ ጨለማ መጣብኝ።

27. በውስጤ ያለው ነውጥ አላቋረጠም፤የመከራ ዘመንም መጣብኝ።

28. በፀሓይ አይደለም እንጂ፣ ጠቋቍሬ እዞራለሁ፤በጉባኤ መካከል ቆሜ ለርዳታ እጮኻለሁ።

29. የቀበሮች ወንድም፣የጒጒቶችም ባልንጀራ ሆኛለሁ።

30. ቈዳዬ ጠቍሮ ተቀረፈ፤ዐጥንቴም በትኵሳት ነደደ።

ኢዮብ 30