ኢዮብ 30:23-27 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

23. ለሕያዋን ሁሉ ወደ ተመደበው ስፍራ፣ወደ ሞት እንደምታወርደኝ ዐውቃለሁ።

24. “የተጐዳ ሰው ተጨንቆ ድረሱልኝ ብሎ ሲጮኽ፣በእርግጥ ክንዱን የሚያነሣበት ማንም የለም።

25. በመከራ ውስጥ ላሉት አላለቀስሁምን?ለድኾችስ ነፍሴ አላዘነችምን?

26. ነገር ግን መልካም ስጠብቅ፣ ክፉ ነገር ደረሰብኝ፤ብርሃንንም ስጠባበቅ፣ ጨለማ መጣብኝ።

27. በውስጤ ያለው ነውጥ አላቋረጠም፤የመከራ ዘመንም መጣብኝ።

ኢዮብ 30