ኢዮብ 3:6-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. ያ ሌሊት በድቅድቅ ጨለማ ይያዝ፤ከዓመቱ ቀናት ጋር አይቈጠር፤ከወራቱ በአንዱም ውስጥ አይግባ።

7. ያ ሌሊት መካን ይሁን፤እልልታም አይሰማበት።

8. ሌዋታንን ለማነሣሣት የተዘጋጁ፤ቀንንም የሚረግሙ ያን ቀን ይርገሙት።

9. አጥቢያ ኮከቦቹ ይጨልሙ፤ብርሃንን እየጠበቀ ይጣ፣የንጋት ጮራ ሲፈነጥቅ አይይ።

10. መከራን ከዐይኔ ይሰውር ዘንድ፣የእናቴን ማሕፀን ደጅ በላዬ አልዘጋምና።

ኢዮብ 3