3. “የተወለድሁበት ቀን ይጥፋ፣‘ወንድ ልጅ ተፀነሰ’ የተባለበት ሌሊት።
4. ያ ቀን ጨለማ ይሁን፤እግዚአብሔር ከላይ አይመልከተው፤ብርሃንም አይብራበት።
5. ጨለማና የሞት ጥላ ይውረሱት፤ደመናም በላዩ ላይ ይረፍ፤ብርሃኑን ጽልመት ይዋጠው።
6. ያ ሌሊት በድቅድቅ ጨለማ ይያዝ፤ከዓመቱ ቀናት ጋር አይቈጠር፤ከወራቱ በአንዱም ውስጥ አይግባ።
7. ያ ሌሊት መካን ይሁን፤እልልታም አይሰማበት።
8. ሌዋታንን ለማነሣሣት የተዘጋጁ፤ቀንንም የሚረግሙ ያን ቀን ይርገሙት።
9. አጥቢያ ኮከቦቹ ይጨልሙ፤ብርሃንን እየጠበቀ ይጣ፣የንጋት ጮራ ሲፈነጥቅ አይይ።