ኢዮብ 3:20-26 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

20. “በመከራ ላሉት ብርሃን፣ነፍሳቸው ለተማረረች ሕይወት ለምን ተሰጠ?

21. ሞትን በጒጒት ለሚጠብቁና ለማያገኙት፣ከተሰወረ ሀብት ይልቅ ለሚሹት፣

22. ወደ መቃብር ሲቃረቡ ደስ እያላቸው፣በሐሤት ለሚሞሉ ሕይወት ለምን ተሰጠ?

23. መንገዱ ለተሰወረበት ሰው፤እግዚአብሔርም በዐጥር ላጠረው፣ሕይወት ለምን ተሰጠ?

24. ትካዜ ምግብ ሆኖኛልና፤የሥቃይ ጩኸቴም እንደ ውሃ ይፈሳል።

25. የፈራሁት ነገር መጥቶብኛል፤የደነገጥሁበትም ደርሶብኛል።

26. ሰላም የለኝም፤ ርጋታም የለኝም፤ሁከት እንጂ ዕረፍት የለኝም።”

ኢዮብ 3