ኢዮብ 3:17-20 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

17. በዚያ ክፉዎች ማወካቸውን ይተዋሉ፤ደካሞችም በዚያ ያርፋሉ፤

18. ምርኮኞች እንደ ልባቸው ይቀመጣሉ፤ከእንግዲህም የአስጨናቂዎቻቸውን ጩኸት አይሰሙም።

19. ትንሹም ትልቁም በዚያ ይገኛል፤ባሪያው ከጌታው ነጻ ወጥቶአል።

20. “በመከራ ላሉት ብርሃን፣ነፍሳቸው ለተማረረች ሕይወት ለምን ተሰጠ?

ኢዮብ 3